top of page
Search

የስኳር ድንች ጥቅሞች



የስኳር ድንች ኃይለኛ በተፈጥሮ ፀረ-ሙቀት አማቂ ነው, በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል በውስጡ የአይረን ንጥረ ነገርን የያዘ መሆኑ ለሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም ከፍ ማለት ጥቅም እንዲኖረው አድርጎታል። አይረን ሰውነታችን በቂ ሃይል እንዲኖረው የሚያግዝ ንጥረ ነገር ሲሆን የነጭ እና የቀይ የደም ህዋሶችን በማጠናከር የበሽታ መከላከል አቅም እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ እርጅናን እና የካንሰር ህመምን ለመቋቋም ይጠቅማል የስኳር ድንች ውስጣቸው በብርቱካናማ ቀለም የበለጸገ መሆኑ ከፍተኛ የካርቶኖይዶች መገኘት ማሳያ ነው፡፡


እነዚህ ካርቶኖይዶች ደግሞ ሰውነታችን ቫይታሚን ኤ እንዲያገኝ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ካርቶኖይዶች እይታችን የተስተካከለ እንዲሆን የበሽታ መከላከል አቅማችን ከፍ እንዲል እንዲሁም የካንሰር ህመም ተጋላጭነትን እና እርጅናን ለመቀነስ ጠቃሚ ናቸው:: የቆዳን ውበት እና ጤንነት ለመጠበ ይረዳል ቫይታሚን ሲ እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎችን ለማከም እና ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን ስኳር ድንች ውስጥም ይገኛል፡፡ ቫይታሚን ሲ ለአጥንት እና ለጥርስ ጤንነት፣ ለምግብ መፈጨት እንዲሁም ለደም ህዋስ መመጣጠን የራሱ ጥቅም አለው፡፡ ከዚህም ባሻገር የቆዳን ውበት እና ጤንነት የሚጠብቅ ሲሆን ሰውነታችን ከካንሰር ጋር ለተያያዘ የበሽታ ስጋት እንዳይጋለጥ ያደርጋል። በመሆኑም በውስጡ ቫይታሚን ሲ የያዘውን ስኳር ድንችን መመገብ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡

ስኳር ድንችን መመገብ ቫይታን 6 የሚያስገኝ ሲሆን ይህ የቫይታሚን አይነት ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ለልብ ድካም የሚያጋልጥ የሆሞሳይስታይን ኬሚካል ያስወግዳል፡፡


የቆዳን ውበት እና ጤንነት ለመጠበ ይረዳል ቫይታሚን ሲ እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎችን ለማከም እና ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን ስኳር ድንች ውስጥም ይገኛል፡፡ ቫይታሚን ሲ ለአጥንት እና ለጥርስ ጤንነት፣ ለምግብ መፈጨት እንዲሁም ለደም ህዋስ መመጣጠን የራሱ ጥቅም አለው፡፡ ከዚህም ባሻገር የቆዳን ውበት እና ጤንነት የሚጠብቅ ሲሆን ሰውነታችን ከካንሰር ጋር ለተያያዘ የበሽታ ስጋት እንዳይጋለጥ ያደርጋል። በመሆኑም በውስጡ ቫይታሚን ሲ የያዘውን ስኳር ድንችን መመገብ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡


225 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page